Abstract
የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ ትምህርታዊ ጨዋታዎችን ተጠቅሞ የማንበብ ክሂልን ማስተማር በተማሪዎች የማንበብ ተነሳሽነት ላይ ያለውን ሚና መመርመር ነው፡፡ ጥናቱ ፍትነት መሰል የምርምር ንድፍንየተጠቀመ ሲሆን አንድ የቁጥጥር ቡድን እና አንድ የሙከራ ቡድን የያዘ ነው፡፡ በእየቡድኑ 35 ተማሪዎች በጠቅላላ 70 ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡ አጥኚው የጥናቱን ቦታና ምድቦችን በአመቺ ንሞና ስልት፤ የክፍል ደረጃን(5ኛ ክፍልን)እና መምህርመረጣን በዓላማ ተኮር ንሞና፤ የጥናቱ ተሳታፊዎችን ደግሞ በጠቅላይ የንሞና ስልት መርጧል፡፡ በመረጃ መሰብሰቢያነትም የቅድመ ትምህርትና የድህረ ትምህርት የማንበብ ተነሳሽነት ደረጃ መለኪያ የጽሁፍ መጠይቆችን ተጠቅሟል፡፡ ትምህርቱ ለ16 ሳምንታት የተሰጠ ሲሆንአጥኚው የሁለቱ ቡድን የማንበብ ተነሳሽነት ውጤቶችንተዛምዶ ለመለየት የፒርሰን የተዛምዶ መወሰኛ ቀመርን ተጠቅሟል፡፡ በተጨማሪም የነፃ ናሞና ቲ-ቴስት ስታትስቲካዊ መተንተኛ ስልትን በመጠቀም በእየቡድኖቹ የተገኘው የቅድመና ድህረ ትምህርት አማካይ፣ መደበኛ ልይይትና የጉልህነት መጠናቸው ተሰልተው ተተንትነዋል፡፡ውጤቱም የቅድመትምህርቱ የተዛምዶ መጠን (r= .067)እና የቁጥጥር ቡድኑ አማካይውጤት(M=51.29)፣ የሙከራው(M= 50.54)ሲሆን፤የጉልህነት ደረጃውም(P= .581) በመሆኑ በሁለቱ ቡድኖች መካከል ጉልህ ልዩነት አለመኖሩን አሳይቷል፡፡ በአንፃሩ በድህረትምህርቱ የታየው የተዛምዶ መጠን(r= - .306) የድህረትምህርቱ አማካይ ውጤት የቁጥጥር ቡድኑ(M=51.77)፣ የሙከራው(M= 55.06) ሆኖ ተገኝቷል፡፡ የጉልህነት መጠኑም (P= .010) በመሆኑ በሁለቱ ቡድኖች የማንበብ ተነሳሽነት ደረጃ መካከል ጉልህ ልዩነት መኖሩን አመላክቷል፡፡ ቁልፍ ቃላትና ሀረጋት : ትምህርታዊ ጨዋታ፣ የተለመደ የማስተማር ስልትና የማንበብ ተነሳሽነት
Talk to us
Join us for a 30 min session where you can share your feedback and ask us any queries you have
Similar Papers
Disclaimer: All third-party content on this website/platform is and will remain the property of their respective owners and is provided on "as is" basis without any warranties, express or implied. Use of third-party content does not indicate any affiliation, sponsorship with or endorsement by them. Any references to third-party content is to identify the corresponding services and shall be considered fair use under The CopyrightLaw.